ቡና ከአልሀሊ 1990
ሊብሮ አርዕስት
- አሰግድ ተስፋዬ (ክፍል 4)
- ፕሪሚየር ሊጉ ሰኞ ይቋረጣል፡፡
- ደደቢትና መብራት - ታላቅ ፍልሚያ
- አሰግድ ተስፋዬ (ክፍል 3)
- መንግሥቱ ወርቁ ( የመጨረሻ ክፍል)
- ጊዮርጊስና ቡና - 130 ደቂቃ - ረብሻና መብራት
- ፊንፌኔ ደርቢ - ለቡና ማሸነፍን አፈላልጉለት
- ብሔራዊ ቡድኑ በብዛት መረጠ
- አሰግድ ተስፋዬ ክፍል 2
- ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያገባ ተመለሰ
- ደደቢት መሪነቱን ተረከበ - አየር ኃይል ተሸነፈ
- ጊዮርጊስ ከውድድር ወጣ - 18 ዓመት
- አሰግድ ተስፋዬ ክፍል 1
- ደደቢት በየቦታው ይመራል - ጌታነህ ተሸሎታል
- ፕሪመየርሊግ - መብራት ኃይል መምራት አልቻለም
ወደ ሊብሮ ገጽ እንኳን ደህና መጡ !
አሰግድ ተስፋዬ (ክፍል 4)
አርብ ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም
ሊብሮ፡- ጨዋ ነኝ ለማለት ነው?
አሰግድ፡- ሣይሆን እኔ ገና ተማሪ ነኝ፡፡ ምንም ነገር አላውቅም፡፡ ጁስ ከመጠጣት በስተቀር ሌላ ምንም አላደርግበትም ስለዚህ ነው የሚተርፈኝ፡፡ ቀለብና መኝታ እንደሆነ ገነት ሆቴል ስለሆነ ችግር አልነበረብኝም፡፡ በደሞዝ በኩል አማርሬ አላውቅም፡፡

ሊብሮ፡- ወደ ትምህርት እንመለስና 12ተኛ ክፍል ነው የገባኸው፡፡ ማትሪክ ነው እና ውጤቱ ምን ሆነ?
አሰግድ፡- ውጤት እንኳን የለም፡፡ የሚያሳልፈኝ ነጥብ አይደለም፡፡ ስለዚህ ኳሱ ላይ በደንብ መግፋት እንዳለብኝ ቆርጬ ገባሁኝ፡፡
አሰግድ ተስፋዬ (ክፍል 3)
አርብ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ.ም
ሊብሮ፡- በአንድ ጊዜ ገብተህ ከሁሉም በለጥካ?
አሰግድ፡- መሆኑ ነው
ሊብሮ፡- ታዲያ ኮከብ ማለት ከሁሉም የበለያ ማለት አይደለም እንዴ?
አሰገድ፡- ግን እኮ እኔ ኮከብ ተጫዋች ተብዬ ብሸለምም ከ2 ሳምንት በኋላ ከሐረርጌ ምርጥ ከ30 በላይ ተጫዋች ሲመረጥ እኔ አልተመረጥኩም
ሊብሮ፡- ኮከብ ተብለህ ለምን?
አሰግድ፡- የሰጡኝ መልስ ያስቃል
ሊብሮ፡- ኮከብ ሆነህ ከተመረጥክ በኋላ ለሐረርጌ ምርጥ ባለመጠራትህ ምን ተሰማህ? የሰጡህስ መልስ ምንድ ነው?
አሰግድ፡ የሚገርምም የሚያስቅም ነው፡፡ እኔ እንኳን ሄጄ አላውቅኩም እኔን የሚያውቁኝ ሰዎች ናቸው ሄደው ጠይቀው የነገሩኝ እኔ ኮከብ ግብ አግቢ ተብዬ ብመረጥ የአጋጣሚ ነው ጎሉን ያገባው ተብሎ ሌሎች ደህና አጥቂዎች ሊመረጡ ይችላሉ፡፡ ኮከብ ተጫዋች ተብዬ ነው የተመረጥኩት፡፡ ስለዚህ ካሉትም አጥቂዎች በእንቅስቃሴም ሆነ በማንኛውም ነገር ትሻላለህ ተብዬ ነው የተመረጥኩት፡፡ የመረጡኝ ደግሞ ትኩረት ስለሰጡኝ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙዎቹ ለሐረርጌ ምርጥ አይመርጡትም የሚል ግምት አልነበራቸውም፡፡ ባለመመረጤ ቅር ባይለኝም ኮከብ ተብዬ የተሰየምኩትን ግን ያፈርሰዋል ብዬ ገምቻለሁ፡፡ እነሱ እኔን ላለመምረጣቸው የሰጡት መልስ ገና ታዳጊ ነው አዲስ አበባ ሄዶ ትልልቆቹን ተጫዋቾች አይችላቸውም፡፡ በዚህ ላይ ስሞታ ቀርቦብናል የሚል ነው፡፡
መንግሥቱ ወርቁ ( የመጨረሻ ክፍል)
ሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2004 ዓ.ም ሊብሮ፡- ሲውዘርላንድ ብቻ ነው የተጫወታችሁት ? መንግሥቱ፡- አይደለም፡፡ እኛ ወደ አውሮፓ ከሄድን ጋሽ ይድነቃቸው የፊፋ አባል ስለሆነ ከብዙ ፌዴሬሽኖች ጋር ትውውቅ ስላለው የተወሰነ ወጪ እያቻሉለት በየሄድንበት ግጥሚያ እናደርጋለን፡፡ አውሮፓ ከሄድን 40 እና 50 ግጥሚያዎች አድርገን ነው የምንመጣው፡፡ ከሲዊዘርላንድ በኋላ ዩጎዝላቪያ ሄደን ብሔራዊ ቡድኑን ገጠምን፡፡ ብሔራዊ ቡድናቸው ያኔ በኦሎምፒክ ውድድር 2ተኛ የወጣ ነበር፡፡ ከአንድ ተጫዋቻቸው በስተቀር ሁሉም ተሰልፈው ነበር፡፡ እስከ እረፍት ጥሩ ተጫውተን 3ለ2 ስንመራቸው ሕዝቡ አበደ፡፡ እንዴት በጥቁር ትመራላችሁ ብሎ በእረፍ ተጫዋቾቹ ሲወጡ በጠርሙስ፣ በድንጋይ ብረት እየገነጠለ መወርወር ጀመረ፡፡ እነርሱም ያ ድንጋጤ ይዟቸው ከእረፍ በኋላ ያ የቀረውን አንድ ተጫዋች አስገቡት፡፡ ልጁ አጥቂ ቦታ ነው የሚጫወተው በጣም ረጅም ነው፡፡ ለእርሱ ክሮስ ሲደረግለት በቴስታ መረብ ውስጥ ማስቀመጥ ጀመረ፡፡ ከዛ እንደገና ክሮስ ሲደረግለት ለጓደኛው አቀብሎ አገቡና በዚህ ዘዴ ብቻ 5ለ3 ተሸንፈን ወጣን፡፡ ዩጎዝላቪያዎች እንደዛ ቀን ደስ ብሏቸው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም ብናሸንፋቸው ኖሮ ሕዝቡ ይገላቸው ነበር፡፡ እንግዲህ ይህ ምን ማለት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረው ቡድናችን ብዙ ጊዜ ከአውሮፓ ቡድኖች ጋ ስለሚጫወት ነበር፡፡ ከዛም ብዙ ጌም እናደርግና አስመራ ሄደን ከአንድ ቡድን ጋር ተጫውተን አቅማችንን እንሞክራለን፡፡
ሊብሮ፡- አስመራ ላይ ብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጊዜ ይጫወት ነበር? መንግሥቱ፡- አዎ ብዙ ጊዜም እዚያ ልምምድ እናደርጋለን፡፡ ለ4ተኛው ለ5ኛው ለ2ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ሁሉ ዝግጅት ያደረግነው እዚያ ነው፡፡ እንዲያውም የማስታውሰው በ2ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ወደ ግብፅ ለመሄድ የልምምድ ግጥሚያ እናደርግ ነበር፡፡ ያ ጨዋታ እርስ በእርስ ነው፡፡ ቡድኑ ገና አዲስ ስለነበር ቦታ ለመያዝ ግድ ስለሆነ የከተማው ስፖርት አፍቃሪ እየመጣ ያን ጨዋታ ያይ ስለነበር ደንበኛ ግጥሚያ ሆነ፡፡ በተለይ እነርሱን ተከላካዮች አልፎ ለመሄድ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሜዳው አሸዋ ስለሆነ በጠለፉህ ቁጥር ወድቀህ ትላላጣለህ፡፡ ያንን ሁሉ መቻል ይኖርብሀል፡፡ ታዲያ ትሬኒንጉን ሊያይ የመጣ ተመልካች የእነርሱን ቡድን ተጫዋቾች ያበረታቱ ነበር፡፡ ሊብሮ፡- የማን ይበዛል?
|





