'>
የኢትዮጵያና የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሱዳን ላይ እየተጫወቱ ነው፡-ኢትዮጵያ 1 ሱዳን 3 አሁን 35ኛ ደቂቃ ላይ ናቸው Arabsat – Ashorooq TV በቀጥጣ እየተላለፈ ነው ማየት ትችላላቹ

ተጨማሪ

መግቢያ ፎርም

Facebook Share

Share on facebook

ቡና ከአልሀሊ 1990

Get the Flash Player To see this player.

ሊብሮ አርዕስት

ወደ ሊብሮ ገጽ እንኳን ደህና መጡ !

አማራጩ ማምለጥ ነው

ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም

በቅጣቱ ጉዳይ ፌዴሬሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ጥፋተኞች በደረጃ ከ1-5 ተቀምጠዋል ነገር ግን ሃላፊነቱን በግልፅ የሚወስድ የለም፡፡ እያንደንዱ እራሱን ነፃ አድርጎ የማምለጥ ነገር ነው የታየው፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው ፅፈጽ ቤቱን ነው፡፡ የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አሻነፊ ዝርዝር ነገሩን ጠቅሰው ለአቶ ብርሃኑ ኮሚኒኬውን አስፈርመው እንደሰጡ፣ ባያስፈርሙም ለአቶ ሰውነት በእርግጠኝነት እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰውነት ምንም ‹‹እንዳልተሰጣቸው አቶ ብርሃኑ ቢደርሳቸው እሳቸውን እንደሚያስውቋቸው እና አቶ በርሃኑ በካርድ ጉዳይ ልጆቹን ቁጥጥር እንደሚያደርግ›› በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተካ አስፋው ‹‹ የፌዴሬሽኑ አሰራር ዝርክርክ ነው ›› ብለው ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ያሉት ነገር ትክክል ነው፡፡ ነገሩን በትክክል ስናየው የፌዴሬሽኑ ጥቅል መረጃ ከፕሬዘዳንቱ እንደተደመጠው ስህተት የሰራነው እኛ ነን አጥፍተናል በሚል ተቅልለውታል፡፡ ስህተት ሰርተናል የሚባለውን ነገር እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የስፖርት ቤተሰቡን ሞራል ገደል ነው የከተቱት፡፡ ህዝቡ ቡድኑን ያበረታታል፡፡ ለነገ ጨዋታ ብርድ እየጠጣ ስታዲየም ስር ነው የሚያድረው፡፡ ባለሀብቱ በፋይናንስ ይደግፋል፣ መንግስት የሚጠየቀውን ሁሉ አሟልቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ግን የዚህን ሁሉ ድጋፍና ሞራል ገደል ከቶታል፡፡ ስህተት ሰርተናል ይቅርታ ይደረግልን ማለት ምን ማለት ነው? እንዲሁ በቀላሉ እቃቃ ጨዋታ አደረጉት እንዴ? ባህርዳር ሰው ሞቷል፣ አዲስ አበባ ብዙ ሰው ተጎድቷል፡፡ የስፖርት ቤተሰቡ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ አንድ ግለሰብ ሰው ገድሎ ተሳስቻለው ይቅርታ ይደረግልኝ ይላል ፡፡ ይቅርታው እንዳለ ሆኖ ሰው መግደሉ ወንጀል ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች በእግር ኳሱ ላይ ወንጀል ነው የሰሩት ወንጀል የሰራ ደግሞ በህግ  ይጠየቃል፡፡ ምንግስት ጥፋተኛውን አጣርቶ ህግ ፊት ማቅረብ አለበት፡፡ ውድድሩ እኮ ፌስቲቫል ሳይሆን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ነው፡፡ ህዝብና መንግስት የብራዚሉን የኣለም ዋንጫ ለማሳካት ተጣምረው ብዙ ሰርተዋል፡፡ የስራው ሁሉ ጫፍና ስሩ ያለው ፌዴሬሽኑ ጋር ነው፡፡ መንግስትም ፌዴሬሽን ባሉት ሰዎች እምነት ጥሎ ነበር፡፡ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የተፈጠረው ስህተት በስፖርቱ ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሏል፡፡ ለምንድነው ጥንቃቄ መሰውሰድ ያልቻሉት ሲባል ዋነኛው ነገር ጥፋት ብንፈፅምስ ምን እንሆናለን፣ማን ይነካናል በሚል ስሜት ነው፡፡ እነሱ ፌዴሬሽኑን የግላቸው አድርገውታል፡፡ አንድ ሰው ብሔራዊ ቡድኑን ሲተች ድክመት እንዲሻሻል ነው ነገር ግን ፌዴሬሽኑም ሆነ አሰልጣኙ ለምን ተነካን ለምንስ ስህተታችን ተነገረን በሚል ተቺውን ኢትዮጵያ አይደለህም በሚል ሰውኑ እያሸማቀቁት ቡድኑን የራሳቸው አደረጉት፡፡ እሺ የራሳቹ ነው ብለን ሰንተዋቸው ደግሞ ይህን አሰፋሪ ስህተት ፈጸሙ፡፡ እስኪ አንዳንድ ነገሮችን እንይ፡፡ የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ቅጣት ያለባቸውን ተጫዋቾች ለቡድን መሪው ለአቶ ብርሃኑና ለአቶ ሰውነት ሰጠሁ ብለዋል፡፡ እንደገና ፊፋ ምንያህል 2 ብጫ ስላለው እንዳታሰልፉ ብሎ ፋክስ እንደላከ አምነዋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ አቶ ብርሃኑ ወረቀቱ እንደደረሳቸው ነገር ግን እንዳላነበቡትና ማን እንደወሰደባቸው (እንደጠፋባቸው ) ተናግረዋል፡፡ ምናልባት የዚህ ወረቀት ጉዳይ የጠፋው የቦትስዋና ወይም የደቡብ አፍሪካ ሰዎች ወስደውባቸው ይሆናል  ምክንያቱም ተጠቃሚዎቹ እነሱ ስለሆኑ፡፡ በሌላ በኩል የግል ስራ እንዳለባቸው እንደተዋከቡ ነው የተናገሩት፡፡ የህዝብ ሃላፊነት ያለበት ሰው የግል ስራ የሚበዛበት ከሆነ ሀላፊነቱን ለሌላ ሰው መስጠት ነው ያለበት ምክንያቱም  አደጋው ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ የሆኑት አሰልጣኙ ናቸው፡፡ ነገር  ግን ከአቶ ብርሃኑ በበለጠ ተጠያቂ መሆን የነበረባቸው እሳቸው ናቸው፡፡ ምክንያቱም አንድ ተጫዋች ሲሰለፍ ጣጣውን ጨርሶ ነው፡፡ ፅህፈት ቤቱ አጠገባቸው ነው፡፡ አሰላለፍ የሚያወጣው ቡድን መሪ ሳይሆን አሰልጣኙ ናቸው፡፡ አሰልጣኙ የሚያሰልፋቸውን ተጫዋቾች ከወሰነ በኋላ ፅህፈት ቤት ሄዶ የነዚህን ተጫዋቾች ሪከርድ ስጠኝ ብሎ መጠየቅና ማረጋገጥ ነበረበት፡፡  ሜዳ ላይ ተጫዋቹ ቢጫ እንደሚያይ ያውቃል እንማን እንዳዩ ላያስተውል ይችላል፡፡ ፅህፈት ቤቱ ቢጫ ያዩትን ተጫዋቾች መዝግቦ እንደሚይዝ ያውቃል፡፡ ከማሰለፉ በፊት ካርድ ያለባቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ፅህፈት ቤቱ አልሰጥህም አይለውም፡፡ አሰልጣኙ አንድ ተጫዋች ሲታመም ከሀኪሙ ያገኘውን ማረጋገጫ ወስዶ እከሌ ብቁ ስላልሆነ አይገባም እከሌ ሀኪሙ ስላረጋገጠልኝ አይገባም ይላል ይህንን የሚያውቀው ጠይቆ ነው፡፡ የተጎዳ ተጫዋችን ማስገባቱ የሚያመጣው ነገር የልም ፡፡ ከሃኪሙ ጉዳት ያለበትን ተጫዋች ጠይቆ ከተረዳ ከፅህፈት ቤት ካርድ ያለበትን (መሰለፍ የማይችለውን) ተጫዋች መጠይቅና መውሰድ ምንድነው ልዩነቱ፡፡ ስለዚህ በዋነኝነት አሰልጣኙ ነው ተጠያቂ፡፡

ጽህፈት ቤቱን በተመለከተ አቶ አሸናፊ እንደገለፁት፡፡ ካርድን በተመለከተ ለአሰልጣኙና ለቡድን መሪው እንዳሳወቁና ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደተወጡ ገልጸዋል፡፡ ምንያህል ጋቦሮኒ ላይ በመሰለፉ ነው ያስቀጣን፡፡ ለመሆኑ እሱ እንዴት ሊሄድ ቻለ? ተጫዋቾች ከሀገር ውጪ ሲሄዱ ፀሐፊው ተጓዦቹን ስም ይዘረዝራል ፕሬዘዳንቱ ይፈርማል ከዚያ ለኤምባሲ ይላካል፡፡ ካርድ ያለባቸው(መሰለፍ የማይችሉት ) ተጫዋቾች ዝርዝር ጽ/ቤት ውስጥ ይገኛል ፡፡ አሰልጣኙ የተጫዋቾቹን ዝርዝር ሲሰጥ ጽ/ቤቱ እከሌ ካርድ ስላለበት መሰለፍ ስለማይችል መሄድ የለበትም በሚል ማስቀረት ይችላል ይህን ደግሞ ጽሃፊውና ፕሬዘዳንቱ ናቸው ማድረግ ያለባቸው፡፡ ይህም እነሱን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ አሁን እኔ ሳስበው ሰዎቻችን ለምንድነው ከፊፋ ጋር ሙግት የገቡት፡፡ ፊፋ ምንያህል 2 ቢጫ ስላለው እባካቹ እንዳታሰልፉት ሲላቸው ምን አገባህ አንተ እኛ ለምናሰልፈው ምን ታመጣለህ ብለው አሰለፉት፡፡ ፊፋ አስጠንቅቆን ወረቀት ሰጥቶን በግድ ካሰለፍን ከጀርባው አንድ ነገር አለ፡፡ ያንን ደግሞ ማጣራት ያለበት መንግስት ነው፡፡ መንግስት ደግሞ አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ብለን እናስባለን፡፡ እነሱ እንዳሉት በስህተት ነው እንዳይባል መስጠንቀቂያውን በእጃቸው ይዘውታል፡፡ ጽ/ቤቱ ከፕሬዘዳንቱ ጋር ተጠያቂ ናቸው፡፡ በ1985 መድን ለአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ሲጫወት ግርማዬ የተባለው ተጫዋች ይኮበልላል በሚል ፌዴሬሽኑ ከሀገር እንዳይወጣ አድርጎት ነበር፡፡ መድን ለኢንተርናሽናል ጨዋታ ስሙን ሲልክ ፌዴሬሽኑ ጠብቆ ይሰርዘው ነበር ያኔ የጽ/ቤቱ ሀላፊ አሁን ያሉት አቶ አሸናፊ እጅጉ ነበሩ፡፡ በዚህ የተነሳ ግርማዬ የመልስ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታ ውጪ ግን መሄድ አይችልም፡፡ ግርማዬ ከሀገር እንዳይወጣ አሳደው ተጠንቅቀው ይሰርዙታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑን የሚጎዳ ካርድ ያለው ተጫዋች መረጃውን በእጃቸው ይዘው ለመቆጣጠር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ ሀገራዊ በሆነ ጉዳይ ለይ ከማሰብ ይልቅ ግላዊ ጥላቻ ላይ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ በ5ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኬኒያና ኡጋንዳ ተደለደሉ፡፡ ዙሩ ሲያልቅ ሱዳን 9 ነጥብ አግኝታ አለፈች፡፡ ኢትዮጵያ 8 አግኝታ ወደቀች፡፡ ኢትዮጵያ ከኬኒያ ጋር ባደረገቸው ጨዋታ ተሸንፋ ነበር፡፡ ኬኒያ 2 የኡጋንዳ ተጫዋቾች አሰልፋ ስለነበር መረጃ አሰባስበው ከሰው ፎርፌ አገኙና ኢትዮጵያ 10 ነጥብ አግኝታ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች፡፡ ያን ጊዜ የነበሩ አመራሮች የራሳቸውን ስህተት ከማረም አልፎ የተጋጣሚያቸውን ስህተት ፈልገው አገራቸውን ይጠቅሙ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የነበሩ አመራሮች ኋላ ቀር ይባሉ ነበር፡፡ አሁን ቴክኖሎጂው በተስፋፋበት ጊዜ እንኳን የተጋጣሚያችንን ስህተት መፈለግ ቀርቶ የራሳችንም ነገር ማጣራት አልቻልንም፡፡

ምንያህል ተሾመን በተመለከተ ዛሬ ከፌዴሬሽኑ በተሰጠው መግለጫ ልጁንም ተጠያቂ በማድረግ ጫና እየፈጠሩበት ሸክሙን ሁሉ እሱ ላይ ለመጫን ያስባሉ፡፡ ምንያህል ስራው ኳስ መጫወት ነው፡፡ ትሬኒንግ ላይ ይሰራል ይደክማል ፡፡ ልጁ በፕሪሚየር ሊግ ቢጫ ያያል፣ በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ከክሉበ ጋር  ተሰልፏል፣ በአፍሪካ ዋንጫ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ተሰልፏል፡፡ በአመት ውስጥ የትና ከማን ጋር ቢጫ እንዳለው ላያስተውል ይችላል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ፊፋ ምንያህል ሁለት ቢጫ ስላየ እንዳይሰለፍ ብሎ የላከው ለሱ ሳይሆን ለጽ/ቤቱ ነው፡፡ የተላከላቸው ሰዎች ጥንቃቄ ሳያደርጉ ምንም መረጃ ያልደረሰው ሰው እንዴት ሊጠነቀቅ ይችላል፡፡ ይህ ሁሉ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የተደረገ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ከደቡብ አፍሪካ ጨዋታ በፊት ዕረቡ ነው ቅጣቱን የሰማነው፡፡ ያላሳወቅነው የህዝቡንም የተጫዋቹንም ሞራል ለመተበቅ ነው ብለዋል፡፡ እውነት እንዲህ የሚያስጨንቃቸው ከሆነ ፊፋ የላከላቸውን እንኳን ይዘው ያንን ነጥብ እንዳይወሰድብን ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

 

አሁን ዋናው ነገር ሀላፊዎቹ ለሰሩት ስህተት እራሳቸውን ከቦታው ያግልሉ፡፡ መንግስት ደግሞ ለሰሩት ወንጀል ተገቢውን ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የነሱ ቅጣት ወደፊትም ለሚመጣው ትምህርት ሆኖ የህዝቡን አደራና ሀላፊነት በትክክል ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ካለበለዚያ ግን ማናለብኝነትና አምባገንነት እይደገ ይሄዳል፡፡ አሁን ዋናው ነገር ፊፋ አታሰልፉ ብሎ መረጃ ሰጥቶ በግድ ካሰለፍን ከጀርባ አንድ ነገር አለ ማለት ነው መጣራት ያለበት ዋናው ነገር ይህ ነው፡፡ ይህ በመንግስት እጅ ነው፡፡ ህዝቡም የሚያውቀውንና የጠረጠረወን ነገር ሊጠቁም ይገባል፡፡

 

ሰዎቹ 10 ሰዓት የገቡ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት አልወጡም

ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ በምንያህል ቢጫ የተነሳ ነጥባችንን ሊቀን በመዘጋጀቱ ከ10 ሰዓት ጀምሮ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ ጋዜጠኞችም ውሳኔውን ለመስማት በአካባቢው ነበሩ፡፡ 10 ሰዓት ላይ ወደ 4 ውስጥ ለመግባት ወላይታ ዴቻና አማራ ውሃስራ እየተጫዉቱ ነበር፡፡ ወላይታ ዴቻ 2ለ1 አሸንፎ ደጋፊዎቹ እየጨፈሩ ሲሄዱ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰዎች ከስብሰባ አልወጡም፡፡ እንደገናም ሌላ 90 ደቂቃ አልወጡም፡፡ የሚወያዩበት ዝርዝር ጉዳይ ባይታወቅም ምንአልባት ማን ነው ጥፋተኛ፣ ምንድነው ለህዘብ ማሳወቅ ያለብን በሚለው ጉዳይ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ምናልባት አንድ ሰው ሊቀጡ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ ነገ ወደ 5 ሰዓት ላይ መግለጫ እንደሚሰጡ ተወርቷል፡፡ ምንያህል ቢጫ አይቶ መሰለፉ እንደተነገረ በህዝቡ ስሜት ላይ ውሃ ነው የቸለሱበት፡፡ በትላንትነው ውጤት ባህር ዳር ላይ 2 ሰው ሞቷል 3 ነጥብ ሲቀነስበት ነፍስ ነው የተከፈለበት፡፡ ለመሆኑ ማነው ተጠያቂ? አሰልጣኙ፣ ተጫዋቹ፣ ቡድን መሪው፣ የፅህፈት ቤት ሃላፊው፣ ቴክኒክ ክፍሉ፣ ህዝብ ግኑኝነቱ፡፡ ፌዴሬሽኑ ዘመናዊ አሰራር መከተሉ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህን ጥቃቅን ግን ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጡ ነገሮችን ችላ ማለት አነበረበትም፡፡  በዓመት ውስጥ 4 ቡድን መሪ ነው የቀያየሩት፡፡ ቡድን መሪ መቀያየሩ በራሱ መረጃዎችን ይዞ ለማሳወቅ ችግር ይፈጥራል፡፡ ቤንች ላይ የሚቀመጡት አሰልጣኞችና ቡድን መሪ ተሰላፊ ተጫዋቾችን አረጋግጦ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ስትጫወት 3 ተጫዋች ቅያሬ ጨርሰን ጀማል እንደተጎዳ ተጠባባቂ በረኛ ተነስቶ ማሟሟቅ ጀምሮ ነበር፡፡ ተመልካቹ ቅያሬ መጨረሳችንን እየጮኸ  ሲናገር ነበር ወዲያው በረኛውም ቁጭ አለ አዲስ ህንፃ በረኛ ሆነ፡፡ ቤንች ላይ ያሉት 4 ተጫዋች መቀየር እንደማይችል ያውቃሉ፡፡ መዋከብ ሲፈጠር ቀላል ስህተቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ የብሔራዊ ቡድን ስታፍ ተጫዋቾች ከማሰለፋቸው በፊት ያለባቸውን ቢጫ አረጋግጠው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንድ ተጫዋች ሲጎዳ ሀኪሙ ሲፈቅድ ነው እንዲሰለፍ የሚደረገው ምክንያቱም የጤንነቱ ሁኔታ የሚረጋገጠው በሀኪሙ ስለሆነ ነው፡፡ ከዲሲፒሊን ጋር በተያያዘ ተሰላፊ የሆኑትን ተጫዋቾች በቅድሚያ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ ምንያህል ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስንጫወት ቢጫ አይቷል፡፡ አዲስ አበባ  ላይ ከቦትስዋና ጋር ስንጫወት ቢጫ አየ፡፡ በቀጣዩ ከቦትሰዋና ጋር ከሀገር ውጪ ሲጫወት ማረፍ ነበረበት፡፡ በዚያ ጨዋታ በመሰለፉ ነው 3 ነጥብ የሚያሰውስደው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ላይ ቡድን መሪው አቶ አፍወርቅ አየለ ነው፣ ቦትሰዋና ላይ ቡድን መሪ የነበረው አቶ ብርሃኑ ናቸው፡፡ አቶ አፍወርቅ ከቡድን መሪነታቸው ቢነሱም የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡ ቡድን መሪዎቹ የኮሚቴ አባል ስለሆኑ ሲለሚገናኙ መረጃ ለመለዋወጥ ችግር አለ ተብሎ አይገመትም፡፡ በሌላ በኩል እነሱ እንኳን በስራ ብዛት ወይም በሌላ ጉዳይ እነዚህን ነገሮች መከታተል ባይችሉ ለህዝቡ መስጠት አለባቸው፡፡ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ዌብሳይት አለው፡፡ የህዝብ ግኑኝነት ቀጥሯል፡፡ የህዝብ ግኑኝነቱ የተሟላ ቢሮ አለው፡፡ እያንዳንዱ ኢንተርናሽናል ጌም አሰላለፉን፣ የጫወታውን ሁኔታ ፣ በጫወታው ከኛም ከባላጋራም የታየውን ቢጫና ቀይ ካርደ ቢያሰፍር የስፖር ቤተሰቡ ዌብሳይቱ ላይ ስለሚያይ እከሌ አንድ ቢጫ ነው፣ ሁለት ቢጫ ነው በቀጣዩ መግባት አይችልም ወይንም አንድ ቢጫ ነው ምገባት ይችላል ብሎ ሊጠቁም ይችላል (በነገራችን ላይ ኢንተርናሽናል ውድድር የሚሳተፉ ክለቦቻችን ህዝብ ግኑኝነቶቻቸው በጫወታው ላይ የታዩትን ካርዶች ማስፈር አለባቸው ምክንያቱም ደጋፊዎቻቸው እንደዚህ አይነት ችግር ሲኖር ሊጠቁሟቸው ይችላሉ)፡፡ ፌዴሬሽናችን ዌብሳይት ቢኖረውም ምንም አይነት መረጃ አያስቀምጥልንም፡፡ ደቡብ አፍሪካ ላይ የተደረገው ጨዋታ በቴሌቪዥን አልታየም ፣ የሄደው አንድ ጋዜጠኛ ነው እሱም ቢሆን ከውድድሩ በፊት ኮበለለ፡፡ ሳላዲን ጎል ማግባቱን ከመስማታችን በስተቀር የስፖርት ቤተሰቡ ስለ ጨዋታው ዝርዝር መረጃውን ባለማግኘቱ፣ ፌዴሬሽኑም ምንም ስላላሳወቀን ምንያህል ቢጫ ማግኘቱን የሚያውቅ ሰው የለም በዚህም የተነሳ ስህተቶች ተፈጥረዋል፡፡ ከቡድኑ ጋር ወደ ውጪ የሚሄዱ ሰዎች ብዙ ነገሮችን ይረሳሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብሔራዊ መዝሙር ካሴቱንም ይዘው የማይሄዱ አሉ፡፡ በ1995 ሞሮኮ ላይ ካሴቱ ጠፍቶ ኖታውም ስለሌላቸው የሞሮኮ ማርሽ ባንድ በጃንሆይ ጊዜ የነበረውን መዝሙር ነው ያሰማው፡፡ ተጫዋቾቹ የሞሮኮ የተዘመረ መስሏቸው ዝም አሉ፡፡ በ1985 ታንዛኒያ ላይ በተደረገው የሴካፋ ውድድር ብሔራዊ ቡድናችን የጀርመን ማሊያ ለብሶ የሱዳን ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመርለት ማንም ሰው ግድ የነበረው አነበረም፡፡ እንደነኚህ ያሉ መታረም የነበረባቸው ነገሮች አድገው ቢጫውንም የሚቆጣጠር ጠፍቶ ዛሬ ዋጋ አስከፈሉን፡፡ ቦትስዋና ላይ የተመደበቸው ኮሚሽነር ሴት ነች፡፡ እንደሚነገረው ምንያህል አንድ ቢጫ ብቻ ነው ያለበት ብላ  ማረጋገጫ ስለሰጠች ተሰልፏል ነው የሚባለው፡፡ የሴትይዋን አላማ ባናውቅም ልትሸውደን ቢሆንስ? ከሷ ይልቅ የኛ ሰዎች ቢጫ የታየበት ሊስት ቢኖራቸው ከሴትይዋ ምንም አንፈልግም ነበር፡፡ በህጉም ደግሞ አወዳዳሪው በኮሚኒኬ ባያሳውቅም አንድ ተጫዋች ሁለት ቢጫ አይቶ ከተሰለፈና ከታወቀ እንደሚያስቀጣ የኛ ሰዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ አሁን ለቀጣዩ ጨዋታ ምንድነው የሚደረገው? አንዳንድ ነገሮችን እንይ፡፡ የደቡብ አፍሪካ ቡድን አምታቶ ለማለፍ እየቆመረ ነው፡፡ የሴንትራል አፍሪካን ቡድን ከኛ ጋር ያለውን ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ እንዲጫወት እያግባባ ነው፡፡ ይህ ማለት ተጫዋቾቹ ጠንክረው እንዲጫወቱ በፋይናንስ ይደግፋል ካሸነፉም ሽልማት ይሰጣል፣ ዳኛም ሊይዝ ይችላል፡፡ የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታ በማጭበርበር ክስ ማስጠንቀቂይ እንደተሰጠው በዜና ማሰራጫም እየተነገረ ነበር፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በዚህ ጨዋታ እጁን ማስገባቱ አይቀርም፡፡ የኛ ፌዴሬሽን በደቡብ አፍሪካ የዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ከአደጋ በመከላከለው በነሱ ላይ ጫና መፍጠር ይጠበቅበታል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት የተወራ ወሬ ነበር፡፡ የሴንትራል አፍሪካን ቡድን ለማጠናከር ከኮንጎና ከቶጎ ተጫዋቾችን በማምጣት ዜግነታቸውን ቀይረው እንዲጫወቱ ደቡብ አፍሪካ ገንዘብ እንዲከፍ ካፍ ህጋዊነቱን እንዲያፀድቅላቸው ሲያመቻቹ እደነበረም ይታወቃል፡፡ ይህ ነገር አጣርቶ የኛ ፌሬሽን አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡ በትላንትናው ጨዋታ ለዶፕንግ የሽንት ምርመራ ተደርጓል፡፡ ይህን ቀን ለምን መረጡት? ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቡድን ባሸነፈ በ1 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የምንያህል ቅጣት ፊፋ በዌብሳይቱ ለቀቀ? መረጃውንም ቀድመው ያሰራጩት የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች ናቸው፡፡  የደቡብ አፍሪካ ቡድን ሀገሩ ሲገባ ደጋፊዎቹ አቀባበል አድርገውለታል፡፡ አቀባበሉን በሁለት መንግድ እንየው፡፡ አንደኛው ያኛን ቡድን በጫወታ ስለበለጡ፣ ሁለተኛው ለቀጣዩ ጨዋታ የተሻለ ተስፋ እንዳላቸው ለማመላከት ይሆን? ይህን ካሰቡ አንድ የሰሩት ሴራ አለ ማለት ነው፡፡ የኛን ፌዴሬሽን ቢሮ መሰብሰብ ሳይሆን ወጣ ብሎ እነሱን ማጨናነቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ አካሄዳቸው በዙ ነገር ለመስራት ያሰቡ ይመስላል፡፡ለነገሩ ካፍና ቻንን የማይለዩ ሰዎች እንዴት ስንት ቢጫ እንደሚያሳርፍ ያውቃሉ ?

 

የዛሬው ጨዋታ

 

 

ቡድናችን ዛሬ አሸነፈ፡፡ ማሸነፉ እንዳለ ሆኖ ሜዳ ላይ የተሻለ ነገር ማሳየት አልቻለም፡፡ አንድ ቡድን በማሸነፉና በመሸነፉ ሳይሆን ተስፋ ሰጪነቱ የሚታየው በያዘው ነገር ነው፡፡ የኛ ቡድን ቢያሸንፈም ምንም ነገር አነበረውም፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ምንም ነገር ስላልነበረን ሄደን ምንም ነገር ማሳየት አልቻልንም፡፡ ያለፍንበት ነገር አሳማኝና ቀጣይነት ስላልነበረው በውጤትም በእንቅስቃሴም የመጨረሻውን ደረጃ ይዘን ተመለስን፡፡ አሁን ለዓለም ዋንጫ የተደለደልንበት ምድም ቡድኖቹ ደካማ ናቸው፡፡ ከዚህ ደካማ ምድብ የተሻለ ደካማ ሆነን ምድቡን መርተናል፡፡ አሁን ለኛ የሚያስፈልገን በቀጣይነት ምን አይነት ቡድን መገንባት አለብን የሚለው ነው፡፡ ከአለም ዋንጫ የአፍሪካ ዋንጫ ደካማ ነው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ብቃታችንን አይተነዋል፡፡ እኛ ምድብ አንድ  የሰሜን ወይም የምዕራብ አፍረካ ጠንካራ ቡድን (ከዚህ በፊት የሚጥሉን) ቢኖሩ እናልፋለን ብለን አንገምትም ነበር፡፡ አሁን ግን ለመሪነት ያበቃን የኛ ጥንካሬ ሳይሆን የምድቡ ደካማ መሆን ነው፡፡ የኛንማ ጥንካሬ አፍሪካ ዋንጫ ላይ አይተነዋል፡፡ ዛሬ በተደረገው ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ በአጠቃላይ ነገር እንደበለጠን የታየ ነገር ነው፡፡ እኛ ጎል አስቆጠርን እንጂ ብልጫ የያዙት እነሱ ናቸው፡፡ የኛ ተጫዋቾች ኳስ ለመቀባበል ሞክረው ነበር ግን አልቻሉም፡፡ ያገኘነውን ለነሱ ነበር የምንሰጠው፡፡ ዛሬ አይታችሁ ከሆነ እነሱ ኳስ ሲይዙ አያያዛቸውና አካሄዳቸው  እኛ ጎል ጋር እንደሚደርሱ ያስታውቃሉ፡፡ እኛ ኳስ ስንይዝ ግን እነሱ ጎል ጋር ሳይሆን እነሱ ሜዳ ጋር መድረስ እንደማንችል ነበር ያሳየነው፡፡ በስታዲየም የነበረው ተመልካችም የተጨነቀው ደቡብ አፍሪካ ኳስ ይዞ ስለተጫነን ነው፡፡ የኛ ቡድን በባለጋራ ላይ ምንመ ብልጫ ሊወስድ የሚያስችለው ነገር አላየንም፡፡ አሁን ወደ ዋናው ነጥብ እንምጣ፡፡ የኛ ቡድን 10 ውስጥ ገባ፡፡ ማን እንደሚደርሰን እስካሁን አላወቅንም፡፡ አይቮሪኮስት፣ ግብፅ ወይም ጋና ሊደርሰን ይችላል፡፡ ግጥሚያው ደርሶ መልስ ነው፡፡ እነ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ በገለልተኛ ሜዳ እንዴት እንዳደረጉን አይታችኋል፡፡ አሁን ደርሶ መልስ ነው የምንጫወተው፡፡ በሜዳችን በደካማው ደቡብ አፍሪካ እንዴት እንደሆንን አይታችኋል፡፡ አሁን ሌላ ሌላ ነገሩን እንተወውና  አይቮሪኮስት ወይም ጋና ጋር በንገናኝ ምንድነው ማድረግ ያለብን? እንዴት ነው መጫወት ያለብን ? በምንድነው እነሱን መብለጥ የምንችለው? እነሱስ በምንድነው የሚበልጡን? ከዚህ ተነስተን ስለ ለውጥ እናውራ፡፡ እኔ የሚገርመኝ የህዝቡ የኳስ ስሜትና ፍቅር እና የቡድኑ የወረደ አቋም አለመገናኘታቸው ነው፡፡ ለዚህ ህዝብ ተስፋ ያለውና አስተማማኝ ቡድን እንዲሰራለት እንመኛለን፡፡

 

ፈልግ

የጎብኚዎች ቁጥር
mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter

ድምጽ መስጫ

የድረገፁ ይዘት
 

Advertisement