ቡና ከአልሀሊ 1990
ሊብሮ አርዕስት
- አካል ብቃትና ብሔራዊ ቡድናችን
- በረኛ በመቀየር ስህተት ማረም አይቻልም - ያልሰሩትን አጭር ኳስ መተግበር አይቻልም
- ድሮና ዘንድሮ
- እንኳን ለ77ተኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ( ቅ.ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ)
- ፉከራ ይቁም
- አንዳርጋቸው ሰለሞን( ክፍል 3)
- የሆላንድ ኮርስ ተጠናቀቀ
- በኦሎምፒክ ሴቶች በወርቅ ይመራሉ
- ቡና ቅዳሜ ልምምድ ይጀምራል
- አዳማ አሰልጣኝ ቀጠረ
- ብሔራዊ ቡድን ተጋበዘ
- 70 ሴቶች ሀዋሳ ከትመዋል
- ብሔራዊ ቡድን እሑድ ሊቢያ ይጓዛል
- መኪና ጠባቂው - ከበረንዳ አዳሪነት እስከ ኦሎምፒክ (ክፍል 2)
- አንዳርጋቸው ሰለሞን( ክፍል 2)
ወደ ሊብሮ ገጽ እንኳን ደህና መጡ !
አካል ብቃትና ብሔራዊ ቡድናችን
ለአለፉት 50 ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ችግር በአካል ብቃት መበለጥ ነው፡፡ ይህን በእውቀት ካልፈታን ለሚቀጥለው 1ሺ አመት ይቀጥላል፡፡ ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች በአካል ብቃት ተጫዋቾችን ብቁ ማድረግ አልቻሉም ተባለ፡፡ ከ38 በላይ የውጪ አሰልጣኞች ቀጥረን ስልጠና ተሰጥቶም በአካል ብቃት ላይ ለውጥ አላመጣንም፡፡ የውጪ አሰልጣኞች የመጡት የእኛ አሰልጣኞች አይችሉም ተብሎ ነው፡፡ ከ1990 ጀምሮ ደግሞ የካራቴ አሰልጣኝ የሆን ዶ/ር ኤሊያስ አብሻክራ የኢትዮጵያ ተጫዋቾችን በአካል ብቃት ለውጥ እንዲያመጡ ላለፉት 15 ዓመታት በርካታ ኮርስ ሰጥተዋል፡፡ ለብሔራዊ፣ ለወጣትና ለታዳጊ ቡድኑ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሆነው ሰርተዋል፡፡ እሳው ደጋግመው እንደሚሉት እኔ ከመምጣቴ በፊት አሰልጣኞች ኢንዱራንስ ብቻ ነው የሚያሰሩት ለመጀመሪያ ጊዜ የአካል ብቃት ስልጣን ለአሰልጣኞች ያስተማርኩት እኔ ነኝ ይላሉ፡፡ ይህን ሀሳባቸውን እንቀበላለን፡፡ ከሳቸው በፊት በኢንዱራንስ፣ እሳቸው መጥተው በአካል ብቃት ተሰርቶ በሁለቱም ጊዜ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ በአካል ብቃ ት ነው የተበለጠው፡፡ ተዘጋጅቶም የሄደው በአካል በቃት ነው፡፡ የተዘጋጀው በአካል ብቃት ከሆነ በዚያ ብልጫ መያዝ አለበት፡፡ ከሌሎቹ የምንሻለው ተጋጣሚዎቻችን ለሳምንት ሲዘጋጁ እኛ ሁለት ወር ውድድር አቋርጠን፣ በር ዘግተን ተጫዋቾችን በእጃችን አድርገን ነው፡፡ የበለጡን ሁለት ወር ሳይሆን ሳምንትም በትክክል ተጫዋቾቹን አያገኙም፡፡ ቡድናችን ሲበለጥ ሁሌም ለምንደንው የአካል ብቃት ችግር አለበት የምንለው፡፡ የአካል ብቃት እንሰራለን፡፡ ነገር ግን የስራው ውጤት በውድድር ላይ ስለማይታይ(ብልጫ ስለማንወስድበት) ሁልጊዜም ‹‹ ስላልሰራን ነው›› እንላለን፡፡ በረጀም ርቀት ሩጫ ውድድር ስለ አካል ብቃት አናነሳም ምክንያቱም ውጤት አለን፡፡ እግር ኳስ ላይ ውጤት ስለሌለን ካለመስራታችን ጋር ነው የሚያያዘው ለስልጠናው ሰው አለን የለንም የሚለው ነገር አይታይም፡፡ ከዚህ ቀደም የበረኛ ችግር በተደጋጋሚ ይነሳል ይህም ችግር የተፈጠረው የበረኛ አሰልጣኝ ስለሌለ ነው ተባለ፡፡ ለብሔራዊ ቡድኑም የበረኛ አሰልጣኝ ተመደበ ለውጥ ግን አልታየም፡፡ ምንድነው ችግሩ ሲባል ብሔራዊ ቡድኑ ለ15 ቀን ነው የሚዘጋጀው በረኞቹ በየክለባቸው መሰልጠን አለባቸው ስለተባለ ሁሉም ክለብ የበረኛ አሰልጣኝ ቀጠሩ፡፡ አሁንም ችግሩ አልተቀረፈም፡፡ አሁን ደግሞ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በየክለቡ ያስፈልጋል እየተባለ ነው ፡፡ በዚህ ደግሞ ውጤቱ ካልመጣ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በየቤቱ ሁሉም ያስፈልገዋል ይሉናል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ ችግር ተንተርሶ ሙያተኞች ስራ ፈላጊ ነው የሆኑት ስራ አግኝተው ለውጥ ቢያመጡ ችግር የለውም ፡፡ የሚሰጠው አስተያየት የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚለውጥ መሆን አለበት፡፡ መፍትሄውንም ሲያስቀምጡ የአካል ብቃት ሰርተን ከተበለጠን እዚያው ውስጥ ከመቦራጨቅ አሰለጣጠኑን በሌላ መተካት ነው፡፡ ምክንያቱም ለእግር ኳስ አስፈላጊ ነው ተብሎ በሚታመንበት ነገር ብልጫ ከተወሰደብን ይሄን በሌላ መተካት ነው፡፡ የአካል ብቃትን መሰረታዊ ነገር አድርጎ መግባት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ፍጥነት ከአካል ብቃት ስራዎች አንዱ ነው፡፡ ፍጥነትን መሰረታዊ ነገር አድርገን ከገባን በዚህ የሚበልጠን ከመጣ እጅ ነው የምንሰጠው፡፡ እኛ በተፈጥሮ በረጅም ርቀት ሩጫ ውጤታማ ነን፡፡ በአጭር ርቀት ሩጫ ውጤታማ አይደለንም፡፡ በረጅሙ ስለሰራን በአጭሩ ስላልሰራን አይደለም ልዩነት የተፈጠረው በተፈጥሮ ነው እንጂ፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በረጅም ርቀት ውጤታማ አይደሉም፡፡ በነገራችን ላይ የናይጄሪያና የጋና ኢንስትራክተሮች ናቸው የኛን አትሌቲክስ አሰልጣኝ የሚያሰለጥኑት፡፡ የጋናና የናይጄሪያ ኢንስትራክተሮች ሀገራቸው ላይ በረጅም ርቀት አሰልጥነው ለኦሎምፒክ ውጤት የሚያመጣ ሳይሆን ሚኒማ ያለው ሰው ማፍራት አልቻሉም፡፡ ነገር ግን በአጭር ርቀት ሩጫ የአፍሪካ ቀዳሚ ሲሆኑ የኦሎምፒክም ተወዳዳሪ ናቸው፡፡ እኛ ለአፍሪካ የአጭ ርቀት ሩጫ ሚኒማ እንኳን የለንም፡፡ እግር ኳስ ፍጥነትና ጉልበት ነው ብለን ከተቀበልን ለዚህ የሚሆን ሰው በተፈጥሮ ያስፈልገናል፡፡ ተፈጥሮን ጥገኛ ባደረገ መልኩ እኛና ናይጄሪያ ስንገናኝ በፍጥነት ማን የተሻለ እንደሆነ የዛሬ 50 ዓመት እናውቀዋለን፡፡ ታዲያ ለምንድነው በአካል ብቃት ስላልሰራን ነው የምንለው? ናይጄሪያ በረጅም ርቀት ሩጫ ስላልሰራን ነው በሚል ለ16 ዓመት በፕሮጀክት አሰልጥነው ሚኒማ ያለው ሩጭ እንኳን ስላጡ አቆሙት በአፍሪካ እንኳን አይወዳደሩም፡፡ ጀርመን በረጅም ርቀት ሩጫ ደካማ ናት፡፡ ውጤት ለማምጣት ከኢትዮጵያ አሰልጣኝ መውሰድ ነበረባቸው፡፡ ግን ለስልጠናው የሚሆን ሰው ስለሌላቸው አሰልጣኝም አልፈለጉም እኛ ግን በአካል ብቃት ሌላውን መብለጥ ስለማንችል የአካል ብቃት ጋጋታ ምን ያስፈልጋል፡፡ በነገራችን ላይ አካል ብቃት የጡንቻ ስራ ነው የጡንቻ ስራ እድገት የለውም ለዚህ ነው አበረታች መድሃኒት የሚወስዱት፡፡ የእውቀት ስራ ግን እድገት አለው ስንፍና ብቻ ነው ሊያስቆመው የሚችለው፡፡ በጂኬ እንቅስቃሴ ከአካል ብቃት ይልቅ እውቀት ላይ ነው የሚያተኩረው፡፡ በጂኬ እንቅስቃሴ አካል ብቀት አያስፈልግም ተብሎ አልተቀመጠም፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ የሚሳተፉ ተጫዋቾች የሚያስፈልግ የአቃም ደረጃ አለ፡፡ ኳስ ስትሰጥ እንዲሁም ስትቀበል የሚያስፈልገውን የአቅም ደረጃ ታውቀዋለህ፡፡ ከሌሎች ቡድኖች ጋር የሚኖረው ልዩነት አካል ብቃትን መሰረታዊ አድርጎ መግባትና አለመግባትን መሰረታዊ ማድረግና አለማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ በዚያኛው ስልጠና ብረት መዝለል፣ መሹለክ፣ ደረት ጀርባ መስራት፣ ሜዳ መዞር፣ የመተጣጠፍ የመወራጨት ልምምድ መስራት እነዚህ ሁሉ የአካል ብቃት ልምምዶች ናቸው፡፡ ውድድር ላይ ግን በዚህ መንገድ ነገሮች አይገኙም፡፡ በጂኬ እንቅስቃሴ በጠባብ ቦታ ሁለት ለሁለት ልምምድ ቢሰሩ 1ኛ በጠባብ ቦታ ነው የሚያስቡት 2ኛ ኳስ ለመቀማማት ቻርጅ ይደራረጋሉ እዚህ ላይ ለጨዋታው የሚያስፈልግ የአካል ብቃት ይገኛል፡፡ ቶሎ ቶሎ ኳስ ለመቀማማት ሲሄዱ ፍጥነት ይገኛል፡፡ ምልልሱ ቶሎ ቶሎ ስለሆነ ትንፋሽ ይገኛል፡፡ ቶሎ ቶሎ ስለሚዟዟሩ መተጣጠፍ ያገኛሉ፡፡ አካል ብቃት ማለት ትንፋሽ፣ ጉልበት፣ መተጣጠፍ ነው፡፡ እነኚ ነገሮች ጠባብ ቦታ ተገኙ፡፡ዋናው ቴክኒኩ ነው፡፡ ጠባብ ቦታ ውስጥ ጨንቅላታቸው የሚያስበው በፍጥነት ነው፡፡ ምክንያቱም የሚቀማ ሰው ቶሎ ቶሎ ይመጣል፡፡ መሸፈን፣ ማቀበል፣ መቀበል፣ ጓደኛ የት ቦታ እንዳለ ማሰብ እነዚህ ሁሉ በጭንቅላት ፍጥነት መስራት አለባቸው፡፡ ባለፈው ሳምንት የብሔራዊ ቡድኑን አይታችሁት የለ የተዘጋን ቦታ ማስከፈት ያልቻለው በጠባብ ቦታ በጭንቅላት መስራት ያለመቻሉ ነው፡፡
በረኛ በመቀየር ስህተት ማረም አይቻልም - ያልሰሩትን አጭር ኳስ መተግበር አይቻልም
ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም ገዛኽኝ የባንክ በረኛ ነው፡፡ በ1995 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ተመረጠ፡፡ ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ፍቃደኛ አይደለም፡፡ ከዚያ በፊት ለወጣት ቡድን ተመርጦ ለሱዳን ጉዞ ፍቃደኛ ሳይሆን ብዙ ጭቅጭቅ ተነስቶ ነበር፡፡ ለኦሎምፒኩ ግን በግድ ትመጣለህ ሲባል አልፈልግም አለ፡፡ ካልመጣህ ትቀጣለህ ሲባል ራሴን አጠፋለሁ አለ፡፡ ይህን ቃል ለሱዳኑም ጨዋታ ተናግሮት ነበር፡፡ ከተቀጣ ከክለቡም ይባረራል ሳይወድ በግድ ከቡድኑ ጋር ወደ አንጎላ ተጓዘ፡፡ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጨዋታ ሳዳት ነበር የተሰለፈው፡፡ ለመልሱ ጨዋታ ሳዳት እጁ ላይ ጀሶ አስገብቶ መጣ፡፡ ሳዳት አልተጎዳም እቤቱ የራሱ ጀሶ ስላለው መሰለፍ በማይፈልግበት ጊዜ ይጠቀምበታል (ማን ሞኝ አለ ፣ማን ይሞታል- ዘሪሁን ተታለለ) ምስኪኑ ገዛኽኝ አንጎላ ሄደ እሱም ሳይፈልግ ነው የሄደው፡፡ አንደኛ በረኛ ሆኖ ገባ፡፡ የተነገረው ያገኘኽውን ለጋ ነው፡፡ ሲለጋ ቶሎ ቶሎ ይመጣበታል፡፡ አሰልጣኙ አውጣ ይላሉ፡፡ ቤንች ላይ ያሉት ተጫዋቾች ጫናውን ፈርተው አውጣን ይላሉ(አምላካቸውን)፡፡ 2ለ0 እየተመራን ገዛኽኝ የለጋው ኳስ እኛ ላይ እየመጣ ጥቃት ስለሚፈፀም ከኋላ ለመጀመር በሚል በቀኝ ላለው ተከላካይ በእጁ ወረወረለት፡፡ ልጁ እሚቀበለው ስላጣ (ልክ ትላንትና ቡርኪናፋሶ ጋር ተከላካዩ የሚቀበለው አጥቶ እንደተነጠቀው) ሰው ስላጣ ለገዛኽኝ ሲመልስለት አጥቂው ሮጦ ስለመጣ ግራ ገብቶት ከፔኔልቲ ውጪ በእጁ ያዘ፡፡
እንኳን ለ77ተኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ( ቅ.ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ)
ዕረቡ ታህሳስ 3 ቀን 2005 ዓ.ም
v ወሩ ታህሳስ ነው ጊዮርጊስ ከተመሰረተ 77 ዓመቱ ነው፡፡ ክለቡ በሀገር ውስጥ ያላገኘው ዋንጫ የለም ሁሉንም ጠራርጎታል፡፡ ነገር ግን እንደ እድሜ ጠገብነቱ በአፍሪካ ክለብ ሻምፒዮና ከምስረታው አንስቶ ላለፉት 49 ዓመት በትጋት ተሳትፎ ዋንጫ አለማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ለዋንጫም ቀርቦ አያውቅም፡፡ በሴካፋም ውድድርም ዋንጫ አላገኘም፡፡ በጥቅሉ ከሀገር ውስጥ የዘለለ ውጤት የለውም፡፡ እንደዛም ቢሆንም እንኳን ለ77ተኛ አመት በዓል አደረሳችሁ፡፡ ባለፉት ረጅም ዓመት አንኳር አንኳር የሆኑ ጉዳዮችን እዚህ ውስጥ ተካቷል፡፡ የክለቡ የምንጊዜም ምርጦችን ሰሞኑን አቋድሳችኋለሁ፡፡
በ1927 ዓ.ም. ዶሮ ማነቂያ ሰፈር የሚገኙት አየለ አትናሽና ጆርጅ ዱካስ የሚባሉ ጓደኛሞች ክለብ ለማቋቋም ሐሳቡን ጠነሰሱ ተስማሙ በቀሪዎቹ ወራት እነሱ ለማቁቋም ያሰቡትን ክለብ ለመቀላቀል የሚፈልጉትን ወጣቶችን ሲያስባስቡ ቆዩ አንድ ቡድን ክለብ መባል ያለበት 11 ተጫዋቾች ሲሟሉ መሆኑን ቁጥሩን እዚያ ለማድረስ ብዙ ጊዜ ፈጀባቸው ቀጣዮ ጉዳዩ የግጥሚያ ማሊያ መግዛት ነበር ገንዘብ አልነበራቸውም ወጣቶቹ ገንዘብ ለማግኘት ቡሄን መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
|





